የኩባንያችን የአለም ገና ቅርንጫፍ ደንበኛ በሆኑት በአቶ ተሾመ መንግስቱ የግል ንብረት በሆነው የከባድ ጭነት መኪና(ሲኖትራክ) ላይ ታህሳስ 17 ቀን 2016 ዓ.ም በተፈጠረው ቃጠሎ ምክንያት በንብረታቸው ላይ ሙሉ በሙሉ ጉዳት ደርሷል፡፡
በዚህም መሰረት ከኩባንያችን በገዙት Political Violence and Terrorism (PVT) ( ውል መሰረት ሐምሌ 26 ቀን 2016 ዓ.ም የ 6,113,810 (ስድስት ሚሊዮን አንድ መቶ አስራ ሶስት ሺህ ስምንት መቶ አስር ብር) የካሳ ክፍያ ፈፅመናል፡፡