Category: Uncategorized
ዜና
የኩባንያችን የአለም ገና ቅርንጫፍ ደንበኛ በሆኑት በአቶ ተሾመ መንግስቱ የግል ንብረት በሆነው የከባድ ጭነት መኪና(ሲኖትራክ) ላይ ታህሳስ 17 ቀን 2016 ዓ.ም በተፈጠረው ቃጠሎ ምክንያት በንብረታቸው ላይ ሙሉ በሙሉ ጉዳት ደርሷል፡፡
በዚህም መሰረት ከኩባንያችን በገዙት Political Violence and Terrorism (PVT) ( ውል መሰረት ሐምሌ 26 ቀን 2016 ዓ.ም የ 6,113,810 (ስድስት ሚሊዮን አንድ መቶ አስራ ሶስት ሺህ ስምንት መቶ አስር ብር) የካሳ ክፍያ ፈፅመናል፡፡
አስደሳች ዜና
ኩባንያችን ብሔራዊ የኢትዮጰያ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ከዚህ ቀድም ሲጠቀምበት የነበረዉን የICT ቴክኖሎጅ በዘመናዊ ቴክኖሎጅ ለማዘመን ከ ARIMA INSURANCE SOFTWARE (W.L.L.) (“ARIMA”) ጋር የውል ስምምነት ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም የተፈረመ ሲሆን የብሔራዊ የኢትዮጰያ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ በመወከል የኩባንው ተጠባባቂ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አለምፀሃይ ደጋጋ እንዲሁም ARIMAን በመወከል አቶ ሞሀመድ ረመዳን በጋራ በመሆን የስምምነት ሰነዱን የፈረሙ ሲሆን በቅረቡ የሲሰተም የማበልፀግ እና የሙከራ ስራ ለመስራት ዝግጅት መጠናቀቁን አብስረዋል፡፡