በ1952 ዓ.ም የወጣው የንግድ ሕግ እንዲሁም የመድን ሥራ ፈቃድ ለመስጠት እና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ቁጥር 88/86 ተሽረው አዲስ ተሻሽሎ ከወጣው የንግድ ሕግ እና የመድን ሥራ ፈቃድ አዋጅ መሠረት በማድረግ የኩባንያችንን የመተዳደሪያ ደንብ እና መመሥረቻ ጽሑፍ ከሕጉ ጋር እንዲጣጣም ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ እንዲሁም የኩባንያውን (መነሻ) ዝቅተኛ የአክሲዮን ሽያጭ ጣሪያ ማስቀመጥ በማስፈለጉ ግንቦት 5 ቀን 2015 ዓ.ም እና መጋቢት 27 ቀን 2017 ዓ.ም በተጠሩ 2 የተለያዩ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔዎች የኩባንያችንን መመሥረቻ ጽሑፍ ተሻሽሎ በሠነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ በቁጥር ቅ8/000978/40/2016 በ10/12/2015 እና ቅ12/ልዩ/0006040/4ለ/2017 ተመዝግቧል፡፡
Author: niceinsurance
የ32ኛው መደበኛ ጠቅላላ እና የ18ኛው አስቸኳይ ጉባኤ አጀንዳዎች

የስብሰባ ጥሪ

የ31ኛው መደበኛ ጠቅላላ እና የ17ኛው አስቸኳይ ጉባኤ አጀንዳዎች

ዜና
የኩባንያችን የአለም ገና ቅርንጫፍ ደንበኛ በሆኑት በአቶ ተሾመ መንግስቱ የግል ንብረት በሆነው የከባድ ጭነት መኪና(ሲኖትራክ) ላይ ታህሳስ 17 ቀን 2016 ዓ.ም በተፈጠረው ቃጠሎ ምክንያት በንብረታቸው ላይ ሙሉ በሙሉ ጉዳት ደርሷል፡፡
በዚህም መሰረት ከኩባንያችን በገዙት Political Violence and Terrorism (PVT) ( ውል መሰረት ሐምሌ 26 ቀን 2016 ዓ.ም የ 6,113,810 (ስድስት ሚሊዮን አንድ መቶ አስራ ሶስት ሺህ ስምንት መቶ አስር ብር) የካሳ ክፍያ ፈፅመናል፡፡


አስደሳች ዜና
ኩባንያችን ብሔራዊ የኢትዮጰያ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ከዚህ ቀድም ሲጠቀምበት የነበረዉን የICT ቴክኖሎጅ በዘመናዊ ቴክኖሎጅ ለማዘመን ከ ARIMA INSURANCE SOFTWARE (W.L.L.) (“ARIMA”) ጋር የውል ስምምነት ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም የተፈረመ ሲሆን የብሔራዊ የኢትዮጰያ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ በመወከል የኩባንው ተጠባባቂ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አለምፀሃይ ደጋጋ እንዲሁም ARIMAን በመወከል አቶ ሞሀመድ ረመዳን በጋራ በመሆን የስምምነት ሰነዱን የፈረሙ ሲሆን በቅረቡ የሲሰተም የማበልፀግ እና የሙከራ ስራ ለመስራት ዝግጅት መጠናቀቁን አብስረዋል፡፡




ታህሳስ 20 ቀን 2016 ዓ.ም በተደረገው የባለአክሲዮኖች 30ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለቀጣይ ሶስት ዓመታት ኩባንያውን ለመምራት የተመረጡ የቦርድ አባላት ዝርዝር

የ30ኛው መደበኛ ጠቅላላ እና የ16ኛው አስቸኳይ ጉባኤ አጀንዳዎች

የ30ኛው መደበኛ ጠቅላላ እና የ16ኛው አስቸኳይ ጉባኤ አጀንዳዎች

እጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት
Details
ብሔራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ.
National Insurance Company of Ethiopia S.C.
ማስታወቂያ
በሥራ ላይ ያለው ቦርድ የሥራ ዘመን እ.ኤ. በ2023/2024 የሂሳብ ዓመት የሚያበቃ ወይም የሚጠናቀቅ በመሆኑ ቀጣዩን የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ ለማከናወን ይቻል ዘንድ ኩባንያው በግንቦት 5 ቀን 2015 ዓ/ም ባካሄደው የባአክስዮኖች 29ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት አስመራጭ ኮሚቴ መመረጡ ይታወሳል፡፡
በዚሁ መሠረት ብሔራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው የመልካም አስተዳደር መመሪያ ቁጥር SIB/48/2019 መሠረት እና በኩባንያው የዳይሬክተሮ ቦርድ የጥቆማ እና ምርጫ አሠራር መመሪያ መሠረት ለዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት ዕጩ ሆነው እንዲቀርቡ የተመረጡትን የተወዳዳሪ ባለአክስዮኖች ሥም ዝርዝር ለኢንሹራንስ ኩባንያው ባለአክስዮኖች እንደሚከተለው ይፋ አደርጓል፡፡
| ተ.ቁ. | የዕጩዎች ሙሉ ስም |
| 1 | ሻለቃ መርዕድ አባተ |
| 2 | አቶ መሠረት ወንድም |
| 3 | አሐዱ ባንክ አክስዮን ማህበር (ተወካይ አቶ ሰፊአለም ሊበን) |
| 4 | ካፒቴን የግዜሩ በለጠ |
| 5 | ፀሜክስ ግሎባል ሀላ/የተ/የግ/ማ (ተወካይ ወ/ሮ ፀደኒያ ረዘነ) |
| 6 | ጀነራል መርካንታይል ሀላ/የተ/የግ/ማ (ተወካይ አቶ ግርማ ከበደ) |
| 7 | ኢንጂ. ታምራት ኢዮብ |
| 8 | አቶ አብርሃም አጥላባቸው |
| 9 | አቶ አየለ አስፋወሰን |
| 10 | አቶ ዘውዱ አስታጥቄ |
| 11 | አቶ ደመረ ደምሴ |
| 12 | ዘመን ባንክ አ.ማ.(ተወካይ አቶ ደረጀ ዘበነ) |
| 13 | አቶ ታምራት ንቁ |
| ተ.ቁ | የተጠባባቂዎች ሙሉ ስም |
| 1 | ኤክስኪዩቲቭ ሆቴል (ተወካይ አቶ እንደሻው ቦጌ) |
| 2 | ኦሞቲክ አጠቃላይ ንግ ሀላ/የተ/የግ/ማ (ተወካይ አቶ ዓለማየሁ ተክሌ) |
| 3 | ብላክ ላየን ሀላ/የተ/የግ/ማ (ተወካይ አቶ አብርሃም ኃ/መስቀል |
| 4 | ደ/ር ወርቅነህ አያሌው |
| 5 | ወ/ሮ ዛዲጓ ፀሐይ |
ማሳሰቢያ
ከላይ በሥም የተገለጹ ዕጩ የቦርድ አባልነት እንዳይወዳደሩ እና እንዳይመረጡ የሚያግድ (የማያስችል) ማስረጃ ካለ የተከበራችሁ ባለአክስዮኖች ማስታወቂያው በጋዜጣ በወጣ በ10 ቀናት ውስጥ በኩባንያው ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 13 በመቅረብ እንድታስታወቁ ኮሚቴው በአክብሮት ይጠይቃል፡፡
ብሔራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ.
የዳሬክተሮ ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ
ሕዳር 19 ቀን 2016 ዓ/ም

