የስብሰባ ጥሪ

   

ለብሔራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ .. ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ብሔራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ አክሲዮን ማኅበር ዋና መ/ቤቱ በቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 04፣ የቤት ቁጥር 894 የሚገኝና የንግድ ምዝገባ ቁጥሩ13-1543/87 ሲሆን የማኅበሩ ዋና ገንዘብም ብር 250 ሚሊዮን የተፈቀደ እና ብር 228 ሚሊዮን የተከፈለ ነው፡፡

ማኅበሩ የባለአክሲዮኖችን 29ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 15ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ቅዳሜ፣ ህዳር 10 ቀን 2015 ዓ.ም.  በሂልተን ሆቴል (Hilton Hotel) ማድረጉ ይታወሳል፡፡ ሆኖም ግን የጉባኤው ቃለጉባኤዎች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ኢንሹራንስ ሱፐርቪዥን ዳይሬክቶሬት ውድቅ በመደረጋቸው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ትእዛዝ መሰረት ጉባኤዎቹን በድጋሚ መጥራት አስፈልጓል፡፡

በመሆኑም የኩባንያው ባለአክሲዮኖች በሙሉ ቅዳሜ ፣ ግንቦት 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ በ2፡00 ሰዓት ጀምሮ በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል (Inter Luxury Hotel) በድጋሚ በሚካሄደው 30ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 16ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንዲገኙ በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀፅ 367/2 መሰረት የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

30ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

  1. የ30ኛውን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎችን ማፅደቅ፤
  2. የ29ኛውን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔዎችን መሻር፤
  3. የተደረጉ የአክስዮን ዝውውሮችን/ድልድሎች፣ ስጦታዎችን እና ሽያጮችን ተቀብሎ ማፅደቅ፤
  4. እ.ኤ.አ. የ2021/2022 በጀት አመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ የስራ ክንውን ሪፖርትን ማዳመጥ፤
  5. እ.ኤ.አ. የ2021/2022 በጀት አመት የውጪ ኦዲተሮችን ሪፖርት እና የሂሳብ መግለጫዎችን ማዳመጥ፤
  6. በተራ ቁጥር 3 እና 4 በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
  7. እ.ኤ.አ. የ2021/2022 በጀት አመት የተጣራ ትርፍ አደላደል እና አከፋፈልን አስመልክቶ የዳይሬክተሮች ቦርድ ባቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
  8. እ.ኤ.አ. የ2022/2023 በጀት አመት የውጪ ኦዲተሮች መምረጥ እና የስራ ዋጋቸውን ተወያይቶ መወሰን፤
  9. የዳይሬክተሮች ቦርድ እ.ኤ.አ. የ2021/2022 በጀት አመት ዓመታዊ ክፍያን እና የ2022/2023 በጀት አመት ወርሃዊ አበል ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
  10. የአስመራጭ ኮሚቴ አባላትን ክፍያ መወሰን፤
  11. እ.ኤ.አ. ለ2023/2024 በጀት አመት ስለሚደረገው የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ የአስመራጭ ኮሚቴ አባላትን መምረጥ፤
  12. የመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤን ቃለጉባኤ ማፅደቅ፡፡

16ኛው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

  1. የ16ኛውን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎችን ማፅደቅ፤
  2. የ15ኛውን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔዎችን መሻር፤
  3. የኩባንያውን ካፒታል ለማሳደግ በ14ኛው ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ የተላለፈውን የክፍያ ጊዜ ውሳኔ በተመለከተ ተወያይቶ መወሰን፤
  4. የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እ.ኤ.አ. በሴፕቴምበር 15 ቀን 2022 ባወጣው መመሪያ (Directive Number SIB 57/2022) መሰረት የኩባንያውን የተከፈለ ካፒታል ስለማሳደግ ተወያይቶ መወሰን፤
  5. የኩባንያውን የመመስረቻ ጽሑፍ ስለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
  6. የአስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤውን ቃለጉባኤ ማፅደቅ፡፡

ማሳሰቢያ፡

  1. በጉባኤው ላይ በአካል ለመገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ተወካይ በመሰየም መሳተፍ ይችላሉ፡፡ ለዚህም ጉባኤው ከሚካሄድበት ቀን ቢያንስ ከ3 የሥራ ቀናት በፊት በኩባንያው ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 13 (ቦርድ ክፍል) በመቅረብ የተዘጋጀውን የውክልና መስጫ ቅፅ በመፈረም ወይም በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት ጽ/ቤት ተረጋግጦ የተሰጠ የውክልና ስልጣን ማስረጃ ዋናውን እና አንድ ኮፒ በስብሰባው ዕለት ይዞ በመቅረብ መሳተፍ ይቻላል፡፡
  • ባለአክሲዮኖችም ሆኑ ተወካዮች ወደ ስብሰባው ቦታ ሲመጡ የራሳቸውን የታደሰ መታወቂያ ካርድ ወይም የታደሰ ፓስፖርት ወይም የታደሰ መንጃ ፈቃድ ዋናውን እና ኮፒ ይዘው መቅረብ እንዳለባቸው እናሳስባለን፡፡
  • ተወካዮች የውጪ ሀገር ዜግነት ያላቸው ከሆኑ ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ እንዲያቀርቡ እንጠይቃልን፡፡

የዳይሬክተሮች ቦርድ

NICE is the first wholly privately owned insurance company, established in post – 1994 Ethiopia, to engage in general insurance business…

Contact Info

Address: Debre Zeit Road ZEFCO Building Kirkos sub-city K.05/06/07 H.No 894
Phone : +251 11 4 705 378/
+251 11 4 704 967
Fax : +251 11 465 0660
P.O.Box:  12645  Addis Ababa, Ethiopia
E-mail: info@niceinsurance-et.com

YouTube
LinkedIn
Share