ብሔራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ. በስራ ላይ ያለው ቦርድ የስራ ዘመን እ.ኤ.አ.
በ2023/2024 የሂሳብ አመት የሚያበቃ ወይም የሚጠናቀቅ በመሆኑ ቀጣዩን የዳይሬክተሮች
ቦርድ አባላት ምርጫ ለማከናውን ይቻል ዘንድ ኩባንያው በግንቦት 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ባካሄደው
የባለአክሲዮኖች 29ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት አስመራጭ መመረጡ
ይታወሳል፡፡
የጉባኤው ቃለ-ጉባኤም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጸድቆ በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ
አገልግሎት ጽ/ቤት የተመዘገበ በመሆኑ አስመራጭ ኮሚቴው ነሐሴ 12 ቀን 2015 ዓ.ም. ስራውን
በይፋ ጀምሯል፡፡
በመሆኑም የኩባንያው ባለአክሲዮኖች ለኩባንያው ዕድገት አስተዋጽኦ ያደርጋሉ ብለው
የሚያምኑበትን ብቁ እጩዎች ከነሐሴ 14 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ህዳር 14 ቀን 2016
ዓ.ም. ድረስ እንዲጠቁሙ አስመራጭ ኮሚቴው በአክብሮት ይጋብዛል፡፡
በብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር ኤስ.አይ.ቢ. 32/2012 መሰረት ተጠቋሚ እጩዎች ማሟላት
ያለባቸው መስፈርቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
- የኩባንያው ባለአክሲዮን የሆነ/የሆነች፤
- የኩባንያው የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሆኖ ኩባንያውን በታማኝነት ለማገልግል ፈቃደኛ
የሆነ/የሆነች፤ - የኩባንያው ሰራተኛ ያልሆነ/ያልሆነች፤
- ዕድሜው/ዕድሜዋ ከ30 ዓመት ያላነሰ፤
- የኩባንያው አስመራጭ ኮሚቴ አባል ያልሆነ/ያልሆነች፤
- በሌላ የፋይናንስ ተቋም ውስጥ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ያልሆነ/ያልሆነች፤
- ከተጠቋሚዎች ውስጥ ቢያንስ 75 በመቶ ከታወቀ ዩኒቨርስቲ ወይም ተቋም የመጀመሪያ
ዲግሪ ያለው/ያላት እና ቀሪዎቹ 25 በመቶ ተጠቋሚዎች ቢያንስ የሁለተኛ ደረጃ
ትምህርት ያጠናቀቀ/ያጠናቀቀች፤ - የስራ ልምድን በተመለከተ በንግድ ስራ አስተዳደር፣ በኢንሹራንሰ፣ በኢኮኖሚክሲ፣ ሕግ፣
በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ የስራ ልምድ ያለው/ያላት ቢሆን ይመረጣል፤ - በአጠቃላይ በብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር ኤስ.አይ.ቢ. 32/2012 ስር የተመለከቱትን
የብቃት እና አግባብነት መመዘኛዎች የሚያሟላ/የምታሟላ፡፡
ማሳሰቢያ፡ - አንድ ባለአክሲዮን እስከ 9 ሰው መጠቆም ይችላል፡፡
- በሕግ ሰውነት የተሰጠው ድርጅት በቦርድ አባልነት ሲጠቆም ድርጅቱን ወክሎ በዳይሬክተርነት
የሚሰራውን ሰው አብሮ መጠቆም አለበት፡፡ - መስፈርቱን የሚያሟላ እና የቦርድ አባል ሆኖ ለማገልገል ፈቃደኛ የሆነ ባለአክሲዮን ራሱን
መጠቆም ይችላል፡፡ - መስፈርቱን የሚያሟሉ ሴት ባለአክሲዮኖች ይበረታታሉ፡፡
- ጠቋሚው ባለአክሲዮን ግለሰብ/ማኅበር/ድርጅት የሚጠቁመውን ባለአክሲዮን ፈቃደኝነት
አስቀድሞ ማወቅ አለበት፡፡ - የመጠቆሚያውን ቅፅ ደብረዘይት መንገድ፣ ዛፍኮ ሕንጻ፣ ሁለተኛ ፎቅ በሚገኘው የኩባንያው ዋና
መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 16 በመቅረብ ወይም ከኢንሹራንሱ ቅርንጫፍ ቢሮዎች ወይም ከኢንሹራንሱ
ድህረ ገፅ www.niceinsurance.et.com ማግኘት ይቻላል፡፡ - ለጥያቄ እና ማብራሪያ ኮሚቴው ፅ/ቤት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥሮች 25114652448
ወይም 251-11-4661129 ወይም 251-11-4705378 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻ
nice@niceinsurance-et.com መጠየቅ ይቻላል፡፡ - የመጠቆሚያ ቅፁ በአግባቡ ተሞልቶ ከተፈረመ በኃላ፤ ማኅበር/ድርጅት ከሆነ ደግሞ ማህተም
ተደርጎበት በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ዛፍኮ ሕንጻ፣ ሁለተኛ ፎቅ በሚገኘው የኩባንያው ዋና
መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 16 በመቅረብ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መክተት ይቻላል፡፡ - የመጠቆሚያ ቅፁ መመለሻ የመጨረሻ ቀን ህዳር 14 ቀን 2016 ዓ.ም. እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት
ድረስ ነው፡፡ ከዚህ ቀን በኃላ የሚደርስ ጥቆማ ተቀባይነት የለውም፡፡
ብሔራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ.
የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ፡፡